• ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ” ማቴ 28፤19

  • ከታሪክ ማኅደር

  • ከታሪክ ማኅደር፦ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አቴና ግሪክ ትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት – ስቶክሆልም

የብፁዕ አቡነ ኤልያስ የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 45ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

የብፁዕ አቡነ ኤልያስ የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 45ኛ ዓመት በዓለ ሢመት የሀገረ ስብከታቸው መንበረ ጵጵስና በሆነው ስቶክሆልም ከተማ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። ዕለቱ ልክ የዛሬ 45 ዓመት ጵጵስና የተቀበሉበት ቀን በመሆኑ ለበዓሉ የበለጠ ድምቀት እንዲኖረው አድርጎታል።
በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የኢጣሊያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ መዊዕ ልሳነወርቅ ውቤ የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፣ …

ለዓሥር ዓመታት ያህል ተለያይተው የነበሩት አድባራት አንድ ሆኑ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት በስዊድን ሉንድ ከተማ ቀደም ሲል ከቅዱስ ሲኖዶስ አንድነት በፊት በተፈጠረ አለመግባት ከዓሥር ዓመታት በላይ ተለያይተው የቆዩት የሉንድ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያምና የሉንድ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚከኤል አብያተ ክርስቲያናት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አረጋዊው ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እና የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች እንዲሁም የሁለቱም አድባራት ካህናትና በርካታ ማኅበረ ምዕመናን በተገኙበት ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. አንድነታቸውን አውጀዋል።

ልዩ የወላጆች ስልጠና ተጀመረ፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ለ8 ሳምንታት የሚቆየው “ዘመኑን የዋጀ ተተኪ ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ትውልድ መፍጠር” በሚል መሪ ቃል ለወላጆች የተዘጋጀው ስልጠና ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓም ተጀምሯል። በመጀመሪያው ቀን ከ325 በላይ ቤተሰቦች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከሀገረ ስብከቱ ውጪም በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ወላጆች ጭምር የተሳተፉበት ስልጠና እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ብጹእ አቡነ ኤልያስ

የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት – ስቶክሆልም ሊቀ ጳጳስ

በፌስቡክ ያግኙን

የሀገረ ስብከቱ አዲሱ የባንከ ቁጥር

Plusgiro፡ 1866938-2
IBAN: SE 28950000996042 186 6938-2
Swift code/BIC: NDEASESS

የዝክረ ነዳያን ባንክ  ቁጥር:

Plusgiro 78 62 90-7
IBAN፡ SE 1795000099604207862907

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት – ስቶክሆልም

  • 08-7492928 / 707302826
  • 427, 12404 Bandhagen, Sweden