የ2016 ዓ.ም ዓመታዊው የጥቅምት መድኃኔዓለም ክብረ በዓል በስቶክሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም መንበረ ጵጵስና ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ::
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ሥቅለት መታሰቢያ የጥቅምት መድኃኔዓለም ክብረ በዓል በስቶክሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም መንበረ ጵጵስና ቤተ ክርስቲያን በማኅሌት፣ በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌልና በሥርዓተ ንግሥ በድምቀት ተከብሯል::
በዕለቱ ከስቶክሆልም፣ ከጎተንበርግ፣ ከኦስሎና ከተለያዩ አጥቢያዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዲያቆናትና ምእመናን በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ተከብሮ ውሏል::