የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በስቶክሆልም ስዊድን በድምቀት ተከብሯል
(መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም ስቶክሆልም ፣ ስዊድን )
የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በስቶክሆልም ስዊድን በድምቀት ተከብሯል።
በዕለቱ ነገረ መስቀሉን የተመለከተ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ ከመሰጠቱ በተጨማሪ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ በስቶክሆልም ከተማ እና አካባቢው በሚገኙት አምስቱም አድባራት ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ያሬዳዊ ዝማሬ ቀርቧል፣ በዓሉን የተመለከቱ መንፈሳዊ ትርዒቶችም በህጸናትና ታዳጊዎች ቀርበዋል።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ከተሰጠ በኃላ በብፁዕነታቸው መሪነት ደመራው ተለኩሷል ።
በበዓሉ ላይ ከሀገር ቤት በእንግድነት የተገኙትን ሊቀ ሊቃውንት ስማዐኮነ መልአክን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰ/ት/ቤት አባላትና የከተማው በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል።