የ2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በኡሚዮ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ !
በስመ አብ፣ ወወልድ፣ወመንፈስ፣ቅዱስ፣፩ዱ አምላክ፣አሜን!!
የተወደዳችሁ አበው የቤተክርስቲያናችን መሪዎችና አገልጋዮች!!
የክርስቶስ ቤተሰቦች፣የእመቤታችን የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች!
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን!!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድን የምድራችን የሰሜን ጫፍ የሆነችው የኡሚዮ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን የመስቀል በዓልን በደማቅ ሁኔታ አክብራለች!!!
በእዚህ አጋጣሚ ከምድር ወገብ እስከ ምድራችን ሰሜናዊ ጫፍ ቤተ ክርስቲያንን በመገንባት፣ርቱዕ የሆነች ሃይማኖታችንን በማስፋፋት የተጉትን፣እንደ ምድር ወገቦቹ እንደ ኡጋንዳው፣እንደ ጅቡቲው፣እንደ ኬኒያው ፣ ያያ መድኃኔ – ዓለም ሁሉ በሰሜን የአዓለም ጫፍ የኡሚዮ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያንን የመሰረቱትን ብፁዕ አባታቻን አቡነ ኤልያስን በልጅነት ዝቅ ብለን ሙሉ ጤናና ረዥም የአገልግሎት ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ እንለምናለን!!!!