የ፳፻፲፮ ዓ.ም የሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በስቶክሆልም መንበረ ጵጵስና ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተካሄደ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስዊድን ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት የ፳፻፲፮ ዓ.ም የሀገረ ስብከቱን ጠቅላላ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ አሚን ለማ በሱፈቃድ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ከየአጥቢያው የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ የተወከሉ አባላት በተገኙበት ጳጉሜን ፩ እና ፪ (September 06/07) በስቶክሆልም መንበረ ጵጵስና ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተካሄደ::
ጉባኤው ጳጉሜን ፩ ቀን በብፀዕነታቸው መሪነት በጸሎተ ወንጌል ተጀምሮ የሀገረ ስብከቱን የ፳፻፲፮ ዓ ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ በልዩ ልዩ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንና እና የሀገራችን ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን በመጨረሻም ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባኤውን በብፁዕነታቸው ጸሎት እና በአባታዊ ቡራኬ ተጠናቋል::