“ሞትንስ የማያይ ማን ነው?“
— መዝሙር 88/89፥48
+++++++++++++++++++++
የተከበራችሁ በሀገራችን ኢትዮጵያ በደቡብ ክልል በጎፋ ዞን የምትገኙ ወገኖቻችን ! በቅርቡ በመሬት መንሸራተት አደጋ
ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጥን በአደጋው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉትን
ወገኖቻችንን ሁሉ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን ። ቤተሰቦቻችሁን በሞት ለተነጠቃችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ብርታቱን
መጽናናቱን ይስጣችሁ በማለት ሀገረ ስብከታችን ጥልቅ ሐዘኑን እየገለጸ ከአደጋው በሕይወት የተረፋችሁ ሐዘተኞች
ወገኖቻችንን በዚህ በቅጽበታዊው አደጋ ወቅት በሚቻለው ሁሉ ከጎናችሁ መሆናችንን ለመግለጥ እንወዳነን።

አባ ኤልያስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በስዊድን፣ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ስቶክሆልም- ስዊድን