በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት -ስቶክሆልም ሊቀ ጳጳስ የመስከረም ወር ሐዋሪያዊ ጉዞ ወደ ሉንድ።
ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ በመስከረም ወር ወደ በሉንድ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ ጉዞ ያደረጉ ሲሆን በሉንድ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም እና በኮፐንሃገን ደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል አቢያተ ክርስቲያናት ትምህርታቸውን ሲተከታተሉ ለነበሩ 8 ታዳጊ ደቀ መዛሙርት መስከረም 12፣ 2017 (September 22, 2014) ማዕረገ ዲቁና ሰጥተዋል፡፡