በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድን ስካንዲናቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በኖርዌ የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ሥር ባለው የአብነት ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የኢጣሊያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሲከታተሉ የቆዩ 15 ታዳጊ ደቀ መዛሙርት በነሐሴ 26፣ 2016/ September 01, 2024 በሀገረ ስብከታችን ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ አንብሮተ ዕድ ሲመተ ዲቁና ተቀብለዋል::